Telegram Group & Telegram Channel
የእኔ ታሪክ (በ አዲስ ምዕራፍ)
ቪቪያን እንደፃፈችው........

የሰው ልጅ ታሪክ መጨረሻ የለውም። ሞት መጨረሻ ነው ብዬ እንዳልደመደም ከሚያደርጉኝ ነገሮች አንዱ ልጅ ነው። የአባቴ ታሪክ እዚህ ላይ ያበቃ ቢመስልም በእኔ እና በአሌፍ ግን ነፍስ ዘርቶ ቀጥሏል። እንዲህ ሆነ.........ወደኋላ ተመልሳ ከአባቷ ጋ ያሳለፈችውን የመጨረሻ ቀን አስታወሰች።

ያቀፏት የሕዝቅኤል እጆች ድንገት ተንሸራተው ሲወድቁ የእርሷም ልብ ላይ የሆነ ነገር ቁርጥ ብሎ ሲወድቅ ታወቃት። ለመናገር ቃላቶች አልነበሯትም አይኗ ብቻ በሚያፈሰው ውሃ ያወራል። ያ ሕይወቱን ሙሉ በመከራ ያሳለፈው ሕዝቅኤል ለዘለዓለም አልተነሳም። ከቁስሉ ሊያገግም ፣ ለብዙ አመት የተከደነው ጥርሱ ሊስቅ ፣ በእንባ ብዛት የሟሙ አይኖቹ እንደገና የተስፋ ጭላንጭል ሊያበሩ በነበረበት ቅፅበት ሕዝቅኤል ድንገት አመለጠ። ከእነሱ ከእናት እና አባቱ፣ ከእህቱ እና ከወንድሙ ጋ ተቀላቀለ....... ህይወት ፍትሃዊ አይደለችም። ያንን ሁሉ የስቃይ እና የመከራ አመታት ሲያሳልፍ ዞር ብሎ ያላየው ሞት...... ለደስታው በተቃረበ ሰዓት ግን ሊወስደው አሰፈሰፈ።

ማቲያስ የተደወለለትን ስልክ አናግሮ ከጨረሰ በኋላ አንድ ጋዜጣ እያነበበ የነበረ ሰው አጠገብ ሄዶ ተቀመጠ። የሰውዬውን ሁኔታ ከላይ እስከታች አጤነው....የሚያውቀው መስሎ ተሰማው ግን የት እንደሆነ ማስታወስ አልቻለም ለዛም ሊያናግረው ፈልጎ ጉሮሮውን ጠራረገ። እንዴት ዋሉ አባ.....? ሰውየው ጋዜጣቸውን ዝቅ አድርገው ወደጠራቸው ሰው ዞር አሉና ፈገግ አሉ። ምኔን አይተህ ነው አባ ያልከኝ ልጄ .......ፂምወትን አለ ቀለል ያሉ ሰው እንደሆኑ ከንግግራቸው ተረድቶ......ቀጠል አድርጎም እርሶስ ምኔን አይተው ነው ልጄ ያሉኝ አለ ጨዋታ ለመፍጠር ያክል.......እሳቸውም ወጣትነትን ብለው ፈገግ አሉ። ማቲያስ እባላለሁ አለ እጁን ለሰላምታ እየዘረጋላቸው፤ ሰውየው ድንግጥ ብለው ማቲያስ አሉ የተዘረጋላቸውን እጅ እየጨበጡ። አወ የእርሶስ አለ ማቲያስ የፊታቸውን መቀየር እያጤነ። የእኔን ስም ነበር ማቲያስ ያልኩህ ማቲያስ እባላለሁ ..........የስማችን መመሳሰል ገርሞኝ ነውኮ መደንገጤ።

ወጣቱ ማቲያስ ወዲያው የሜሮን የቀድሞ ፍቅረኛ አእምሮው ላይ ብልጭ አለ። ጋሽ ሕዝቅኤል ጓደኛወት ነው? አብርሃምም?.....ሽማግሌው ደነገጠ ማነህ አንተ?..............መጀመሪያ ጥያቄዬን ይመልሱልኛ.... አወ ማን ነህ?......የሜሮን ልጅ.........በእድሜ ብዛት የማያረጀወሰ የሽማግሌው ማትያስ ፍቅር ስሟን ሲሰማ እንደገና አገረሸ። ወጣቱን አስተዋለው እውነትም እሷን ይመስላል ..........እኔኮ አመጣጤ ሕዝቅኤል መታመሙን ሰምቼ ነበር......አለ አሁንም ድንጋጤው እንደወረረው። ና ወደውስጥ ጋሽ ሕዝቅኤልንም እየው እማዬም አለች.........ተያይዘው ወደውስጥ ገቡ።.......ሲገቡ ግን የሕዝቅኤል አይኖች ከሚወደው ጓደኛው ከማትያስም በቅፅበታት ቀድመው ተከድነዋል።

ሆስፒታሉ ሌላ ድባብ ሞልቶታል ቃል የሞላው ቃል አልባ እንባ ከየ አቅጣጫው ይፈሳል ማቲያስ በቁሙ ራደ። ሀዘን ሀዘን ብቻ ተነበበ። ሁሉም የምሬት እንባውን ያነባል......የአሌፍ ግን ቃልም አለው። ለዚህ ነው እንዳውቅህ ያደረግከው? ትተኸኝ ለመሄድ...አባ ለምን? እስከዛሬ ትናፍቀኝ አልነበረ? ስታገኘኝ ጥለኸኝ ለመሔድ ነበር?

ግን ሆነ ሕዝቅኤል ላይመለስ አይኖቹ ተከደኑ። የሚወዱትም ነፍሶች ላይጠገኑ ተሰበሩ። ስርዓተ ቀብሩም ራቢያም ራሷ በተገኘችበት ተፈፀመ።ራቢያ ለዚህ ሁሉ አመታት አፍና የያዘችውን የስቃይ እንባ በመቃብሩ ላይ ዘረገፈችው አልቅሳ አልቅሳ አልጠገበችም አትጠግብምም። አለመኖሩን ሳታይ አምና የነበረችው ራቢያ አይታ ስታረጋግጥ ግን ለመቀበል አልቻለችም አቃታት።

ኤልሳ ልትናገር ይቅርና መቆም አቅቷት ለቀብሩም በሰወች ተደግፋ ነበር የመጣችው። የመጨረሻ ቃሏ " ላልድን ሰበርከኝ አይደል?" የሚል ነበር ከዛ ቃል በኋላ ከ አፏ የወጣ አንድም ቃል የለም። የእሷም አንደበት ከ ህዝቅኤል ጋር ተቀበረ።

ቪቪያን ውስጧ ነው የሚያወራው አይኗ ደግሞ በእንባ ቃላቶቹን ያወጣል። ብቻ ግን ስትታይ ከማዘን አልፎ ሕመሟ ይጋባል ።
ጓደኛው ማቲያስ ቪቪያንን አይቷት ውስጧን አነበበው። እንደ ሕዝቅኤልም ሊጠብቃት ለራሱ ቃል ገባ።
ሁሉንም ሰው በአንድ ላይ የሰበረ ቀን.....

ይቀጥላል ........

@nibab_lehiwot
@nibab_lehiwot
@nibab_lehiwot

tg-me.com/nibab_lehiwot/196
Create:
Last Update:

BY ሕይወትን - በገፅ

Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 283

Share with your friend now:
tg-me.com/nibab_lehiwot/196

View MORE
Open in Telegram

ሕይወትን በገፅ Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

Unlimited members in Telegram group now

Telegram has made it easier for its users to communicate, as it has introduced a feature that allows more than 200,000 users in a group chat. However, if the users in a group chat move past 200,000, it changes into "Broadcast Group", but the feature comes with a restriction. Groups with close to 200k members can be converted to a Broadcast Group that allows unlimited members. Only admins can post in Broadcast Groups, but everyone can read along and participate in group Voice Chats," Telegram added.

Importantly, that investor viewpoint is not new. It cycles in when conditions are right (and vice versa). It also brings the ineffective warnings of an overpriced market with it.Looking toward a good 2022 stock market, there is no apparent reason to expect these issues to change.

ሕይወትን በገፅ from ms

Telegram ሕይወትን - በገፅ
FROM USA